ቤኒሻንጉል ጉምዝ ዘላቂ መፍትሄን ይሻል

Posted by Badr Ethiopia on

ቤኒሻንጉልጉምዝ ዘላቂ መፍትሄን ይሻል 

   በሀገራችን በተለያዩ ክልሎች የንጹሀን ዜጎች ህይወት በአሰቃቂ ሁናቴ በግፍ እየተቀጠፈ መገኘቱና ስቃዩን በራሱ መስማት እጅጉን እንደሚያሳዝን በተለያዩ ጊዜያት ባወጣናቸዉ መግለጫዎች መግለጻችን ይታወቃል።  

  በቤንሻንጉል ጉምዝ በተለያዩ ጊዜያት ዘርን ተኮር ባደረገ መልኩ የበርካታ ንጹሀን ዜጎች ህይወት በግፍ እየተቀጠፈ ነዉ ። ከተለያዩ አካላት በርክት ያሉ ዜናዎች (መረጃዎች) ቢቀርቡም በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚፈጸመዉ ህገ ወጥ ግድያን አስመልክቶ ለሚሰነዘሩ ምክንያቶች ግን በማንኛዉም መስፈርት ተቀባይነት የሌላቸው የእኩይ ባህሪ ተግባር ዉጤት በመሆናቸው በድር ኢትዮጵያ ድርጊቱን በጽኑ ያወግዛል።

    የዜጎችን መብት የማስጠበቅ ተግባር በቀዳሚነት የመንግስት አካል እንደሆነ ቢታመንም የአካባቢዉ ህብረተሰብ ችግሩን ለመቅረፍ ብሎም ዘላቂ መፍትሄ ለመሻት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለዉ ይታመናልና ለዘመናት የነበረዉ አብሮነት ሊዳብር እንጂ በጥቂት ግለሰቦች ላይ በተመሰረተ ፍላጎት የማህበረሰቡን አንድነት ሊያናጉና ሊያደፈርሱ እንደማይገባ ለመግለጽ እንወዳለን ።

   በቤንሻንጉልጉምዝ በተደጋጋሚ በንጹሀን ዜጎች ህይወት ላይ የተፈጸመዉን ጥቃት መንግስት ተከታትሎ ዘላቂ መፍትሄ ከመሻት ባለፈ በጥቃቱ የተሳተፉ ግለሰቦችም ሆነ አካላት ለህግ እንዲቀርቡ በማድረግና ለማህበረሰቡም በቂ የሆነ መረጃ በመስጠት ሊከናወን እንደሚገባ ለመግለጽ እንወዳለን። 

በሀገራችን ሰላምን ለማስፈን የሁሉም ዜጋ በጎ ተሳትፎ ወሳኝ ነዉ።

በድር ኢትዮጵያ    ሰሜን አሜሪካ     ዴሰምበር 27 2020                       


← Older Post Newer Post →