ዶክተር አብይ አህመድ አሊ የኖቤል የሰላም ሽልማት ተሸላሚ በመሆናቸው ከበድር ኢትዮጵያ የተሰጠ የደስታ መግለጫ!

Posted by Badr Ethiopia onimage.png
image.png
በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነዉ
 
ዶክተር አብይ አህመድ አሊ  የኖቤል የሰላም ሽልማት ተሸላሚ በመሆናቸው ከበድር ኢትዮጵያ  የተሰጠ የደስታ መግለጫ!
 
ዶክተር አብይ አህመድ አሊ  የኖቤል የሰላም ሽልማት ተሸላሚ በመሆናቸው በድር ኢ ትዮጵያ የተሰማውን ደስታ በድርጅቱ መሪወችና በአባላቱ ስም የተሰማውን ደስታ ለኢትዮጵያ መንግስና ሕዝብ በኩራትና በተስፋ ይገልጻል። 
 
ይህ ዓለም ዓቀፍ የበጎ እይታ ግንዛቤ ለአገራችን ሕዝቦችና ፖሊቲከኞች የመልካም መንፈስ መፍለቂያና ማጠናከሪያ እንዲሆንም በጽኑ እንመኛለን።
 የዶክተር አብይ አህመድ ለዚህ እድል ተመራጭ መሆን ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም ኩራት ነው።
 
ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ ወደ ስልጣን ከመጡበት እለት ጀምሮ  በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ የነበረውን ሽኩቻና አለመረጋጋት ለማርገብና ሰላምን ለማስፈን ብዙ ደፋ ቀና ያሉና የጣሩ ብሎም የተሳካላቸው ባለ ብሩህ ተስፋና የሩቅ ሃሳብ የሰነቁ መሪ ናቸው። 
ሰላም ባንድ ስው ብቻ ብሩህነትና ሰላም ፈላጊነት እይገኝምና የፓሊቲካ ፓርቲዎች ፣ የክልል አስተዳዳሪወች፣ የሃይማኖት መሪወች፣  የሲቪክ ድርጅቶች፣ያገር ሽማግሌዎች እንዲሁም በአህጉር ደረጃ ያገር መሪወችን ትብብርና ድጋፍ ይጠይቃል።
ስለዚህም አብረናቸው በመቆም ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር የበኩላችንን ድርሻ እንድንወጣ በድር ኢትዮጵያ ዓለም ዐቀፍ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ድርጅት ጥሪውን ያቀርባል።
በድር ኢትዮጵያ ሰሜን አሜሪካ
አክቶበር 11 / 2019
 

← Older Post


Leave a comment

Please note, comments must be approved before they are published.