Deprecated: Non-static method JSite::getMenu() should not be called statically, assuming $this from incompatible context in /home/badrtube/public_html/badrethiopia.org/oldsite/templates/yoo_revista/warp/systems/joomla/layouts/com_content/article/default.php on line 13

Deprecated: Non-static method JApplication::getMenu() should not be called statically, assuming $this from incompatible context in /home/badrtube/public_html/badrethiopia.org/oldsite/includes/application.php on line 536

Ye Wileta Milash

Posted in Amharic Articles

Sunday Jan 27, 2013| Huda Mohammed | Facebook

በአላህ ስም/አአወ

የውለታ ምላሽ

እኔን ጨምሮ ለሀገሬ ህዝብ ትላንትም፣ ዛሬም ነገም በጥቅሉ ዘመናት ያልሻረው ባለውለታ የሆነ ምስኪን የቤት እንሰሳን ለዛሬው መልዕክቴ በማነጻጸሪያነት ልወስደው ግድ አለኝ፡፡ ምክንያቱም የሚፈጸምብንን ላም ባልዋለበት…ድንበር አልባ ግፍ በጥቂቱም ቢሆን ሊያሳይልኝ ይችላልና ነው፡፡

ይህ የቤት እንስሳ በሬ ነው፤ አዎ አንጋፋው የኢትዮጵያውያን ዘመን ያልሻረው የዘመናት ባለውለታ…በሬ! የበሬን እሮሮ ለበሬ ፋንታ ልበለው? “እድሜ ለጨቋኝና አምባገነን ነገስታት/መንግስታት/ ይሁንና እነሱ ህዝባቸውን በተለይም ሙስሊሙን በመጨቆን ህዝቡ/ሙስሊሙ/ ደግሞ አልጨቆንም በሚል ፍልሚያ መካከል ዕውቀትና ልማት ቦታ ተነፍገው ኋላቀርነትና ድህነት የሀገሪቱ መገለጫ በመሆኑ አለም በዘመነበት በአሁኑ ወቅት የኔ ትከሻ በህይወት ሳለሁ ይሞታል፡፡” በሬው ተናግሮ ቢደመጥ ከዚህም የባሰ የሚል ይመስለኛል፡፡

እኔ ግን አንድ ጥያቄ አለኝ፤ እሱም የበሬ ውለታው ምንድን ነው? የሚል ነው፡፡ የተለያየ መልስ ልትሰጡ ትችላላችሁ፡፡ ብትስማሙም ባትስማሙም የኔን መልስ ወረድ ብዬ አሰፍራለሁ፡፡ 

በነገራችን ላይ በዚህ ጽሁፍ የበሬን ውለታ ማስተማር እንዳልሆነና ይሄ ለሁላችንም ግልጽ እንደሆነ እረዳለሁ፡፡ ይህን ለማስተማር ብደክም ልጅ ለናቷ…ይሆንብኛል፡፡ ዋናው አላማዬ ለመልዕክቴ በማነጻጸሪያነት ለመውሰድ ቁጥር አንድ ተመራጭ ሆኖ ስላገኘሁት ነው፡፡ 

 አርሶ አደሩ በሬን ለዕርሱ በሚሰጠው ጥቅም እና ጥቅም ብቻ ነው የሚያሰላው፡፡ ልብ አድርጉ አርሶ አደሩ በዚህ ስሌት መንቀሳቀሱ ስህተት ነው የሚል ነገር አልወጣኝም፡፡ በሬ ታከተኝ፣ ሰለቸኝ፣ አሁን አሳርፈኝ…ወዘተ የማለት አንደበት የለውም በተግባር ለማሳየት ቢሞክርም መብት የለውምና በጅራፍ እየተገራ በህይወት ዘመኑ ሁሉ ቀምበርና ሞፈር ጎትቶ በእንግልቱ አርሶ አደሩን ብሎም የኢትዮጵያን ህዝብ ለዘመናት እየመገበ ይገኛል፡፡ 

የተወለደ ቀን ለዚህ ተግባር የታጨው ጥጃ ቀምበር መሸከም እስከሚችልባት የአንድና የሁለት አመት እድሜው በነጻነት ይለቀቃል፡፡ከዚህ እድሜው አንስቶ እስከ ህይወት ፍጻሜው የአርሶ አደሩን ማሳ በማረስ፣ እህል በመውቃት፣ ምርቶችን በተጎታች ጋሪ ከቦታ ቦታ በማዛወር፣ ቤት ሲገነባ ጭቃ በማቡካትና በመሳሰሉት ተግባራት ያገለግላል፡፡ በዚህ ሂደት ለድካሙ ካሳ አይጠይቅም፤ በርግጥ በበሬው ብዙ መጠቀም የፈለገ ብልህ ገበሬ ጥሩ አድርጎ ይቀልበዋል፤ በዚያው ልክም ይገለገልበታል፡፡ ከዚህ ውጪ ካሳ አይጠይቅም፣ አይወቅስም፣ ቂም አይዝም…ወዘተ፡፡ በድምሩ በሬ ለህዝባችን ከቤት እንስሳት መካከል ግንባር ቀደም ባለ ውለታ ነው፡፡ 

ታዲያ የዚህ በሬ የውለታው መጨረሻ ምንድን ነው? ሽልማት ነው? ጡረታ ነው? ዬለም አይታሰብም፤ የበሬ የውለታ መጨረሻው ቢላዋ ነው፡፡ መታረድ ነው፡፡ ምክንያቱም ትላንትም ዛሬም አገልግሎት እንዲሰጥ ነው የታቀደው፡፡ የበሬውና የአርሶ አደሩ ግንኙነት ይህና ይህ ብቻ ነው፡፡ የውለታው መጨረሻም ህይወቱን ሰጥቶ ለአርሶ አደሩ ሌላ ተጨማሪ ውለታ መዋል ነው፡፡

እህስ ምን ይጠበስ? ለበሬው ከዚህ የተለየ ሊደረግለት ይገባ ነበር እንዴ? የሚለው የብዙዎቻችሁ ጥያቄ ሊሆን እንደሚችል እንደሚገባም አምናለሁ፡፡ ትክክል ነው የበሬው እጣ ፈንታ ከዚህ የተለየ ሊሆን አይችልም፡፡ ካልተሳሳትኩ እንሰሳትም ሆኑ እጽዋት የሰው ልጅን እንዲያገለግሉ የተፈጠሩ በመሆኑ በህይወታቸውም በሞታቸውም የሰው ልጅን ቢያገለግሉ ተገቢ ነው፡፡ ወቀሳ መሰንዘር ካለበት በአምባገነንና በግፈኛ አገዛዛቸው የተነሳ ህዝባችን በነጻነት አስቦ እውቀትና ጉልበቱን ለልማት አውሎ አለም ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ እንዳይደርስና ዛሬም በኋላ ቀር የአስተራረስ ዘዴ ወይም በበሬ ትከሻ ላይ ጥገኛ ሆኖ ለዘመናት የረሀብና የድህነት ምሳሌ የሆነች አሳዛኝ ሀገር እንድትኖረን ያደረጉና እያደረጉ የሚገኙ ሁሉ በዘመን ተሻጋሪ ታሪክና ትውልድ ሲወቀሱ ይኖራሉ፡፡

በኢትዮጵያችን ውስጥ የበሬው/የእንስሳው/ ታሪክ በእኛ በሙስሊሞች ዛሬ እየተፈጸመ አይደለምን? ዛሬ የሙስሊሙ ውለታ እንደ በሬው ቢላዋ ጥይት አልሆነምን? በእርግጥ ኢህአዴግ እኛ ላይ የበሬውን አይነት /የእንስሳና የሰው ልጅ ግንኙነት/ መብት የለውም፡፡ እኩል ዜጎች ነን፡፡ ሁለታችንም እኩል መብት ሁለታችንም እኩል ግዴታ ሊኖረን ግድ ይላል፡፡ ይሁን እንጂ አሁን ያለው እውነታ ይህን ያሳያልን? በፍጹም አያሳይም ጭላንጭሉን እንኳን አያሳይም፡፡ እኛና ኢህአዴግ በተግባር የአርሶ አደሩና የበሬው ግንኙነት እንዲኖረን ነው እየሰራ የሚገኘው፡፡ ኢህአዴግ ትግል ብሎ የሚገልጸው ይህን ነው፡፡ እኛ ትግል ብለን የምንገልጸው ከሰው ተቆጥረን የዜግነት መብቶቻችንን አግኝተን እስከነ ሙስሊምነታችን በሰላም እንኑር የሚለውን ጥያቄ ነው፡፡

ኢህአዴግን ልክ እንደበሬው አገልግለነዋል፤ በቅንነት በማገልገል ላይም እንገኛለን፡፡ መንግስት ነውና የህዝብ አካል ሆነን ለ22 አመታት በላባችን ለካድሬዎቹ ደሞዝ እየከፈልን እንገኛለን፡፡ ኢህአዴግ ጥሪ ባቀረበባቸው የሰላም፣ ዳር ድንበር የማስከበርም ሆነ የልማት አጀንዳዎች ሙስሊሙ ወደኋላ ያለበት አጋጣሚ የለም፡፡ እምነታችን ለሰላምና ለልማት ትኩረት ሰጥቶ የሚያስተምር በመሆኑ ለዚህ መሰል ጥሪ ወደ ኋላ ልንል አንችልም፡፡ ህልውናውን ሊያጣ ቋፍ ላይ በደረሰባቸው አጋጣሚዎች በአመዛኙ በሙስሊሙ ድጋፍ የአመራር ዘመኑን ሲያራዝም ኖሯል፡፡ ችግር ውስጥ በገባባቸው አጋጣሚዎች የሙስሊሙን ድጋፍ ሲያገኝ የኖረው ሙስሊም ባልሆነው ወገናችን የደረሰው የአገዛዝ ግፍና በደል ስላልደረሰበት ሳይሆን ለእምነት ነጻነቱ ቅድሚያ የሚሰጠው ህዝበ ሙስሊም ከቀድሞ ስርአቶች የተሻለ መብት ያገኘ መስሎ ስለተሰማው ሌሎች በደሎችን በሁለተኛ ደረጃ አይቶ መሸከምን በመምረጡ በውሳኔ የከፈለው መስዋእትነት ነው፡፡ ለዚህና መሰል መልካም አገልጋይነቱ ካሳ አልጠየቀም፤ አገልግሎቱ በዛብኝ፣ ሰለቸኝ፣ ይቀነስልኝ፣ እነዚህ ጥቅሞቼ ይከበሩልኝ አላለም፡፡ ያለው ነገር ቢኖር በሙስሊምነቴ ላይ እንድዘወትር ተወኝ ነው፡፡

ሙስሊሙ እምነትህን ልቀቅ እስከተባለበት አምና ድረስ ለአስርተ አመታት ኢህአዴግ መጅሊስን ከሙስሊሙ በመንጠቅ በመደባቸው ካድሬዎች ያሻው ግፍ ሲፈጸምበት ስቃዩን ዋጥ አድርጎ በነበረው ጠባብ እድል እምነቱን ሲተገብር ኖረ፡፡ የዛሬ አመት በይፋ ለተከፈተው ጥቃት በግድ እምነቴን እንድለቅ ለምን እገደዳለሁ ብሎ በሰላማዊ መንገድ ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎችን በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ቢያቀርብም ምላሹ እንደምናየው ነው፡፡

ልክ እንደበሬው ኢህአዴግ ህዝበ ሙስሊሙን ለዕርሱ በሚሰጠው ጥቅም እና ጥቅም ብቻ ነው የሚያሰላው፡፡ ስልጣንን ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ትከሻው እስከሚላጥ ድረስ ሲያርስበት በውጤቱም ስልጣኑን ሲያደላድልበት ኖሯል፡፡ ዛሬ ደግሞ በእርዱ ለመጠቀም ቢላዋውን ሲስል ከርሞ በገሀድ መሰንዘር ከጀመረ አመት አስቆጥሯል፡፡ ሙስሊምነትን ለመንጠቅ ከማስገደድ የበለጠ መታረድ ከቶ ምን ሊኖር ይችላል?

እኮ ምን ሊኖር ይችላል? ለህዝበ ሙስሊሙ ከዚህ የከፋ የውለታ መልስ ሊኖረው እንደማይችል ዕሙን ነው፡፡ ከሚገዛው እኩል ሰው ሆኖ፣ ከሚገዛው እኩል ዜጋ ሆኖ፣ አብሮ ባረቀቀው ህግ በፍሀዊነት መተዳደርና መዳኘት መብቱም ግዳታም ሆኖ ሳለ እንደ ሀገር ለሁሉም እኩል የወጣችውን ጸሀይ/ህገመንግስት/ እንዳይሞቅ በኢህአዴግ ሰራሽ በደል ተጋርዳበት ማንነቱን ከማጣት የበለጠ ሞት ምን አይነት ሞት ይኖራል?

ይህን እርድ በበጎ ፈቃዱ የሚቀበል ዜጋ ይኖራል እንዴ? በሬውስ ቢሆን እርዱን በጸጋ ይቀበላል እንዴ? ምስኪን በሬ አላህ ሰትሮበት ቀድሞ ስለማያውቅ ተጠልፎ ከተጋደመ በኋላ ነው ራሱን ለማዳን የሚታገለው፡፡ ቀድሞ የሚፈጸምበትን ቢገነዘብ ኖሮ ተመሳሳይ አቋም ይወስድ ነበር እንዴ? ለኔ በሬ/እንሰሳ/ ነውና ተመሳሳይ አቋም ቢወስድም አይገርመኝም፡፡ አፈጣጠሩም ለዚሁ ስለሆነ የአላህን አምር ለመፈጸም ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ነው የምደርሰው፡፡

እኛስ? የዛሬው ትውልድ? በቁርአን “ወለቀድ ከረምና ያበኒ አደመ” የተባልነው? “ወማኸለቅቱል ጂኒ ወልኢንሲ ኢላ ሊያዕቡዱን” የተባልነው? ስንኖር ኢህአዴግን አገልግለን እርዳችን በኢህአዴግ ሊፈጸም ሲሆን መልሳችን ምን ይሆናል? ትግል ውስጥ ያለን አላህ ቁዋውን ይጨምርልን፤ ለመብታችን ሰላማዊ ትግል በማድረጋችን ምክንያት የግፍ በትር የደረሰብንና እየደረሰብን የምንገኝ አላህ እጥፍ ድርብ ምንዳውንና ጽናቱን ይለግሰን፡፡ የተለያዩ የግል ምክንያቶችን አኑረን እየታረድን/ሙስሊሙ እየታረደ/ ዝምታን የመረጥን ግን ከበሬው በምን እንሻላለን? ሰው ሆነን ተፈጥረን እንደ በሬ ኖረን እንደ በሬ እንድንታረድ የሚተላለፍ የሰው ልጅን/የአቅመ ቢሱን/ ውሳኔ በጸጋ የምንቀበል ካለን ዋ! ለኛ! ወደ ፊት የታቀደውን እያወቅን ባለማወቁ ምክንያት ከታረደው በሬ ካልተሻልን፣ እምቢ ለእምነቴ ካላልን፣¸የተመዘዘውን ስለት ወደ አፎቱ ማስመለስ ካልቻልን ቢያንስ አቅማችን በፈቀደው ሁሉ ካልታገልን በዱንያም ተዋርዶ ከመኖር አኼራንም ከመክሰር የተለየ ዕጣ ፈንታ ሊኖረን ይችላልን? ለሚደርሰው የትውልድ ኪሳራ አላህ ፊት ከኢህአዴግ ያነሰ ተጠያቂ ልንሆን እንችላለን? መልሱን ለእያንዳንዳችን በተናጠል ትቸዋለሁ፡፡ አላሁ አእለም

ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች

አለሁ አክበር

About Us

WHAT WE DO

 • Da'awa
 • Unity
 • Advocancy
 • Development

Departments

 • Da'awa
 • Media
 • Finance
 • Convention
 • Community Relations
 • Badr Sisters
 • Youth
 • Ethiopian Relations
 • International Relations
 • Marriage