Condolences - Sheikh Mohammed Siraj

Posted in Articles and Press Releases

Nov 26, 2015 | Badr Ethiopia

ጥልቅ የሀዘን መግለጫ

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን

ታላቁ ሼህ መሀመድ ሲራጅ ማርሶ ሳሊህ አላህ ለጄነት ይበላቸዉና ወደ አሄራ ሄደዋል። ሼህ መሀመድ ስራጅ ከአባታቸዉ ሥራጅ ማርሶ ሳሊህ እና ከእናታቸዉ ከወ/ሮ መና ኑሩ በ 1343 ዓመተ ሂጅራ በሰፈር ወር 15ኛዉ ቀን በራያ አካባቢ ተወልደዉ በሰፈር ወር 13ኛዉ ቀን በ 1437 ዓመተ ሂጅራ በ 94 ኛዉ እድሜያቸዉ ሞቱ። ሼህ መሀመድ ሲራጅ በሀገር ዉስጥ በታለያዩ አካባቢ በመዘዋወር የዲን እዉቀትን የተማሩ ሲሆን በቁርዐንና ተፍሲር እንዲሁም ፍቂህ እና ኡሱል ሰርፍ እና ነህዉ በላጋ ቀርተዋል። ከሀገር ዉጭም በየመን እንዲሁም በመካ የዲን ትምህርታቸዉን ተከታትለዋል። በኋይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት የፓርላማ ተመራጭ በመሆን ለበርካታ ዓመታት ካገለገሉ በኋላ በየመን ሀገር የኢትዮጵያ ኤምባሲ አምባሳደር ሆነዉ በሹመት ተልከዋል። ከዚያ በኋላ መካ ላይ ራቢጣቱል አለመል ኢስላሚ ሙስተሻር(አማካሪ) በመሆን ሰርተዋል። ድርጅቱንም በመወከል ወደ አሜሪካ ተልከዉ በኒዉዮርክ ሲያገለግሉ ቆይተዉ የአገልግሎት ጊዜያቸዉን ሲያጠናቅቁ ዲሲ አካባቢ ኑሮአቸዉን መስርተዉ በፈርስት ሂጅራ ፋዉንዴሽን ኢማም እና የዳዋ ክፍል ሀላፊ ሆነዉ አገልግለዋል። በድር ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት ሲቋቋም ( ስያሜዉን ጨምሮ) በተለያዩ ስቴቶች በመዟዟር ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞችን በማጠናከርና የዳዕዋ ትምህርት በመስጠት ልዩ አስተዋጽኦ ያደረጉ ታላቅ ሼህ ነበሩ። በህመም የአልጋ ቁራኛ እስከሆኑ ድረስ ዲናቸዉን የሀደሙ፤ ሙስሊሙን ማህበረሰብ አንድ የሚሆንበትን የዲን አስተምሮ እያከናወኑ ኖረዋል። በስተመጨረሻም ቨርጂኒያ አካባቢ ሰፈር 13ኛዉ ቀን ረቡእ እለት በ 1437 ዓመተ ሂጅራ በ 94 ዓመታቸዉ በሞት ተለይተዋል። አላህ (ሱወ) የሄዱበት አገር አላህ ያሳምርላቸዉ !!! አላህ (ሱወ) የሄዱበት አገር ከነበሩበት አገር የተሻለ እና የተመቻቸ ያድርግላቸዉ !!! ከዋህሸተል ቀብር አላህ ይጠብቃቸዉ !!! በድር ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት ለቤሰቦቻቸዉና ለዘመዶቻቸዉ አላህ (ሱወ) መጽናናትን እንዲሰጣቸዉ ይመኛል። 

Press Release over the Unjust Court Decision on the Ethio-Muslims Arbitration Committee and Others

Posted in Articles and Press Releases

Press Release in PDF version

የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የተላለፈውን ኢፍትሃዊ የፍርድ ውሳኔ በሚመለከት ከበድር ኢትዮጵያ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

وَيَمْكُرُونَ وَيَمْكُرُ اللَّهُ ۖ وَاللَّهُ خَيْرُ الْمَاكِرِينَ

 “…ይመክራሉም አላህም ተንኮላችውን ይመልስባቸዋል፤ አላህም ከመካሪዎች ሁሉ በላይ ነው።” አል-አንፋል (8:30)

የተራዘመ የፍርድ ሂደት የፍርድ ጉደለት ነው እንደሚባለው ሁሉ፤ ለሦስት ዓመት ሲጓተት የቆየው የኮሚቴዎቻችን የፍርድ ጉዞ ይኸውና እንዲህ  አሳዛኝና አስደንጋጭ አንዲሁም መላ ሙስሊሙን በሚያስቆጣ መልኩ የፍርድ ጉድለትንና የሙስሊሙን ሕገመንግስታዊ የመብት ጥያቄ ባላገናዘበ መልኩ ተወስኗል። ይህ ውሳኔ የሙስሊሙን ማሕበረሰብ ሰላማዊና ሕጋዊ ትግል በኣሸባሪነት ቀለም ቀልሞ የህዝቡን ሰነልቦናዊ ግንዛቤና የህሊና ንቃት ለማሽመሽመድና እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ዳግም መብቱን እንዳይጠይቅ ታቅዶ የተበየነ የፖሊቲካ ድራማ ሲሆን፤ ሙስሊሙ ማሕበረሰብ ግን ከመቼውም ጊዜ በላይ  አንድነቱን አጠናክሮና ሰላማዊነቱን  ጠብቆ  ትግሉን  በማጠናከር  ያነሳቸውን  የመብት ጥያቄ ሙሉ በሙሉ እስኪመለሱለት እና ወክሎ የላካቸው መሪዎቹ እስኪፈቱ ድረስ ያለመታከት ይታገላል።

በድር ኢትዮጵያ የሙስሊሙ ጥያቄ በሰላማዊና በመነጋገር እንዲፈታ ከመንግስትም ሆነ ኮሚቴው ጋር መገናኘቱ ይታወቃል። መንግስት ከሙስሊሙ ጋር ያለውን ቅራኔ አለዝቦ መፍትሄ በመሻት መላ ሙስሊሙን ለእድገትና ብልጽግና በጥሩ መንፈስ እንዲያሰልፈው ሊያግባቡ የሚችሉና መተማመንና መግባባት የሚፈጥሩ እርምጃዎች እንዲወሰድ ጠይቀን ነበር። አሁንም ቢሆን ሕዝበ ሙስሊሙ በመንግስትና በፍትህ ስርአቱ ላይ ሙሉ በሙሉ  ተስፍ እንዲቆርጥ  ካልተፈለገና የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ፤ እንዲሁም በሃገሪቱ እድገትና ብልጽግና መርሃ ግብር ላይ በሙሉ ፍላጎት ተሳታፊ እንዲሆን ከተፈለገ ፤ ከፍርዱ ባሽገር የሚወዳቸውን መሪዎቹን በማንኛውም መልኩ በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱና ከሚወዳቸው ማሕበረሰብና ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊና ሕጋዊ ለመብትና ለእምነት ነጻነት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሁሌም በአላህ (ሱ.ወ) ፍቃድ ህያው ሁኖ ይኖራል። የመሪዎቹ በነጻና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር መለቀቅ ለአገር ሰላምና መረጋጋት፤ ለእድገትና ብልጽግና ይበጃል ብለንም እናምናለን። በዱዓ፤ በሃሳብና፤ በስሜት፤ ከኮሚቴዎቻችንና ከቤተሰቦቻቸው ጋር አብረን የምንቆም መሆናችንን በድር ኢትዮጵያ አሁንም ያረጋግጣል።

አላህ (ሱወ) በጽናትና በጥበብ ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንቅስቃሴ አጋር እንድንሆን ችሎታና ትዕግስት እንዲስጥን እንለምነዋለን።

በድር ኢትዮጵያ አለምአቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት
የዳይሬክተሮች ቦርድ
ሰሜን አሜሪካ 
August 2015

About Us

WHAT WE DO

 • Da'awa
 • Unity
 • Advocancy
 • Development

Departments

 • Da'awa
 • Media
 • Finance
 • Convention
 • Community Relations
 • Badr Sisters
 • Youth
 • Ethiopian Relations
 • International Relations
 • Marriage