በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነዉ

 

 

 

 

                    

                        በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነዉ

የአንዋር መስጊድ ቃጠሎ በተመለከተ

         በአንዋር መስጂድ ላይ የተፈጠረዉን የእሳት ቃጠሎ ስናይ ልባችን በጣም አዝኗል። ምንም እንኳን በአሁኑ ሰዓት የቃጠሎዉ መንስኤ በዉል ባይታወቅም የሀይማኖት ተቋማት ሊኖራቸዉ የሚገባ ከበሬታ በቃል ብቻ ሊገለጽ የሚችል ባይሆንም የእኛነታችን መገለጫዎች መሆናቸዉ ይታመናል።

   የአንዋር መስጂድ የህዝበ ሙስሊሙ ብሎም የሀገር ታሪካዊ ቅርስ እንደ መሆኑ መጠን ልዩ  ትኩረት ተሰጥቶት ሊጠበቅ እንደሚገባ ይታመናል። የደረሰዉም የእሳት ቃጠሎ ምክንያቱ ተጣርቶ በመንግስት በኩል  ለህዝብ ግልጽ ይደረጋል ብለንም እናምናለን። በዚያ ድቅድቅ ጨለማ እሳቱ ወደ ሌላ ቦታ እንዳይዛመት እንዲሁም ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠርና ለማጥፋት በህዝቡ የተደረገዉ ርብርቦሽ እጅግ በጣም አስደሳች ነዉ፤ ዋናዉን የመስጂድ አካል ከቃጠሎ ለመታደግም ተችሏል።

     ለማንኛዉም የህዝብ ንብረት በሆኑ የእምነት ተቋማት ላይ የሚደረገዉ ልዩ ጥበቃም ሆነ ተቋማቱን ከሌሎች ጉዳዮች ጋር ተያያዥነት እንዳይኖራቸዉ ተደርገዉ እንዲዋቀሩ ቢደረግ ብሎም ወደፊት በሚከናወኑ ግንባታዎች ሁሉ ቢታሰብበት መልካም እንደሆነ ለመግለጽ እንወዳለን።

                                       በድር ኢትዮጵያ

                                       ሰሜን አሜሪካ

                                       ጁን 28, 2018