logo

     

ለውድ ነገር ዘወትር ውድ ዋጋ ይከፈልበታል!

ታሪክን የሚክዱ፥ከራሳቸዉ የአመጣጥ ታሪክ እነኳን ለመማር ይታክታቸዋል። ወያኔ ከዛሬ ጥቂት ኣመታት በፊት ከሰባት በማይበልጡ ጀግና የትግራይ ልጆቼ ከደርግ ጋር ትግል ጀመርኩኝ፤ ኣሰራ ሰባት አመታትንም ታግዬ ለድል በቃሁኝ ሲለን፤ በአንጻሩ ግን ትላንትና እነርሱ በሰባት ሰዎች ትግል ማድረጋቸውና ኢትዮጵያን መቆጣጠራቸው እጅጉኑ ሊያስገርማቸው ይችል ይሆናል።

ነገር ግን ብርቅዬ፤ የሰላም፤ የእድገት፤ የብልጽግናና አብሮ መኖርን ላስተማሩት አምባሳደሮች ነገ ይህ ታሪክ ለስላም ፈላጊዎች ይሳናቸዋል ብሎ ማሰቡ የራስን ታሪክ መካድ ብቻም ሳይሆን፤ከዘመናት በፊት እስልምና በምን ይህል ሰዎች በአላህ ትእዛዝ ተጀምሮ ዛሬ ከማንኛዉ በአለም ላይ ካሉት ሀይማኖቶች በሚያስደንቅ ፍጥነት እያደግ መጥቶ ዛሬ የደረሰበትን ደረጃ ብቻ መመልከቱ ታሪክ ብቻም ሳይሆን፤ በእጅጉ ልንማርበት የሚገባት ትእይንት ነበር፤ ነገር ግን የተፈለገውን ያክል ቢደከምና ሙስሊሙ ማህበረሰብ ምንነቱንና ማንነቱ በግልጽ ለማስቀመጥ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቢቆይም፤ እነሆ ይህንን የራሳቸውን እውነታ የካዱ የዛሬው የሀገር መሪዎች ነን ባዮች ሊገነዘቡትና ሊረዱት አላቻሉም፤ እንዲችሉ ቢመከሩም ቢዘከሩም ለመሆን ግን አልፈቀዱም።

ዛሬ በእስር ላይ የሚገኙትን መልእክተኞች የፖለቲካ ፍርድ መስጠት ለታሳሪዎች በፍርዱ ወቅት፤ ፈራጁም ተፈራጁ ልብ ያልነዉ ነገር ቢኖር፤ ታሳሪዎቹ ፍርዱን ቀድመዉ የተነበዩትና ለመቀበልም የደስታ ምልክት ከፊታቸው የተነበበዉና ፈራጁን ጭምር ያስደመመዉና ይስገረመዉ እንዲሁም የታሪክ አሻራ ጥሎ ያለፈዉ እንዲሁ ዝም ብሎ ሳይሆን፤የሚከተሉትን ጽንሰ ሀሳቦች በጥልቀት ከመረዳት ለተግባራዊነቱም መስዋእትነት ለመክፈል ካለዉ ዝግጁነት ነዉ:-

-ዉድ ነገር ዉድ ዋጋ ይከፈልበታል፥ የአላህ ጀነትም ዉድ ናት ዉድ ዋጋም ታስክፍላለች!
-ይህቺ ኣለም ለሙእሚኑ እስር ቤት ናት፥ለከሃዲያን ግን ጀነት (ገነት) ናት !
-እስልምና እንግዳ ሆኖ እንደመጣዉ ሁሉ እንግዳ ሆኖ ያልፋል !
-በሃይማኖት ማስገደድ የሚባል ነገር የለም !
-ከሃዲያን ይወዱናል አትበሉ፥መቸዉንም ሊወዱዋችሁ አይችሉም፤ የእነርሱን መንገድ እስካልተከተላችሁ ድረስ !

ውድ የሙስሊሙ መብት መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎቻችንም ይህንን ታላላቅ ጽንሰ ሃሳቦች በእጅጉ ከጅምሩ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ማስተማር ብቻ ሳይሆን፤ ለመተግበርም ጸንተዉ የተነሱ የዚህ ክፍለዘመን የሙስሊሙ ብርቅዬ ትውልዶች ብቻም ሳይሆኑ፤ ታማኝ የኢትዮጳያ ንጹሃን ዜጎች መሆናቸዉን ለመላዉ አለም በእጅጉ እስገንዝበዋል፤አስተምረዋል።

የትላንትናውን ሶስትና አራት መሰረታዊ ጥያቄዎችን አንመልስም ሲባል፤ነገ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለሚጠይቃቸው አስርና መቶ እጥፍ ጥያቄዎች ከውዲሁ እንድትዘጋጁ ግድ ይላቸሗል።

ዞሮ-ዞሮ ከሃገር ኖረዉ-ኖረዉ ከአፈር እንደሚባለው ሁል የፈለግነው ይክል ስልጣና ሀብት ማከማቸት መቻላችን ከዚህች አለም ለዘላለም ለመኖር ዋስትናን አይሰጥም።

የኢትዮጵያን ሙሲሊም እንደትላንቱ የኣጸዎች ዘመን ረግጠን እነገዛለን ብለው ዛሬም እንደታላንቱ የሚያስቡ ካሉ፤ ዛሬም የምነለው ነገር ቢኖር:- ታላንትና ማለት ዛሬ ማለት አይደለም!

ዛሬም እንደታላንቱ ለግዢው ኣካል የምንለው ነገር ቢኖር ከሙስሊሙ የታሪክ ሂደትና የእድገት ፍጥነት መማር ቢሳናችሁ ከራሳችው የትግል ሂደትና የታሪክ ኡደት ተምራችሁ: የሙስሊሙን ህገመንግስታዊ የመብት ጥያቄውን አስራ ሰባት ሰዎችን በማሰርና የፖለቲካ ፍርድ በመወሰን የተጠየቀዉን ህገ መንግስታዊ ጥያቄ መጨፍልቅ ይቻላል ከሚል እንድምታ ተቆጥባችሁ ሰዓቱ ከመርፈዱ በፊት የፖለቲካ ዉሳኔን ወደ ጎን ትታችሁ እዉነተኛ ፍርድ በመስጠት የሙስሊሙን ህገመንገስታዊ የመፍትሄ ኣፈላላጊዎች በነጻ እንድታሰናብቱ በድር እትዮጵያ አለም ዓቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት ጥሪዉን ያስተላልፋል።

                                 በድርእትዮጵያአለምዓቀፍየሙስሊሞችድርጅት

ሰሜንአሜሪካ

ኦገስት 4 ቀን 2015