እንኳን  1439ኛው ዓመተ ሂጅራ ለተከበረው ታላቁ የረመዷን ወር በሰላም አደረሳችሁ

 

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነዉ

 

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُون

 

    እናንተ ያመናችሁ ሆይጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ህዝቦች) ላይ እንደተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነገገ ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና (2183)

 

    የአላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ እዝነት ሆኖ ለዚህ ለተቀደሰ ወር በመድረሳችን አላህን እያመሰገንን የዘንድሮው ረመዳን ለመላዉ ሙስሊም ማህበረሰብ የሰላም የነጻነት የእድገት  እንዲሁም ከጀሀነም እሳት ነጻ ወጥተን ጀነት የምንገባበትን ኸይር የምንሸምትበት  እንዲያደርግልን  አላህን እየለመንን እንደወትሮዉ ሁሉ በዚህ ረመዳን ለተቸገሩ ሁሉ አቅማችን በሚችለው መጠን በመድረስ እና አላህ በሚወደው ቦታ ላይ ሁሉ በመገኘት ለበለጠ ኸይር ስራ እንድንነሳሳ መላውን ሙስሊም እህት ወንድሞቻችንን አደራ ማለት እንወዳለን ሰላሜ ይረጋገጥልኝ  እኩልነትና የሃይማኖት ነጻነቴ ይከበርልኝ በማለታቸው ምክኒያት ለእስር ተዳርገው ብዙ የሮመዳን ወሮችን  በእስር ቤት በስቃይ ካሳለፉ በኃላ ተፈተው ከህዝባቸውና ከቤተሰባቸው ጋር የተከበረውን ወር ለመታደም በመቻላቸው ፈጣሪያችን አላህን እያመሰገንን አሁንም በየክልሉ በእስር ላይ የሚገኙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ከእስር ተፈተዉ አላህ በሰላም ከሚወዳቸዉና ከሚያፈቅራችዉ ማህበረሰብና ቤተሰብ ጋር እንዲቀላቅላቸዉ በዱዐ እንድንበረታ እያሳሰብን  

  በዚሁ አጋጣሚ ምንም እንኳን የሰላማዊ ትግላችን መሪዎች ከግፍ እስር በመፈታታቸው ብንደሰትም እነሱም ሆነ ሌሎች ብዙዎች የሞቱለት የታሰሩለት እና በስደት የተንገላቱበት መሰረታዊ ጥያቄዎቻችን ስላልተመለሱ ዛሬም ከትግሉ  መሪዎቻችን ጋር  አጋር በመሆን የምንችለውና የሚጠበቅብንን ለማበርከት የሚረዳን የኢማን ጥንካሬ የምንጨምርበት የበረካ ወር እንዲሆልን አላህን እንማጸናለን።      

ወሩን በሰላም ጀምረው በሰላም ከሚጨርሱትና ተጠቃሚ ከሚሆኑት እንዲያደርገን ብሎም እንዳችን ለሌላችን ዱዐ በመደራረግ ከማይጠገበው የፈጣሪያችን ራህመት እንድንቋደስ በተከበረው ወር የተከበሩ በሆኑ ኢባዳዎች ላይ እንድንበረታ ለማሳሰብ እንወዳለን ::

አላሁ አክበር 

 

ዳሪ ሀምዛ

ፕሬዚደንት