በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነዉ

        

 

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُون

    እናንተ ያመናችሁ ሆይጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ህዝቦች) ላይ እንደተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነባ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና ። (2፡183)

  የአላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ እዝነት ሆኖ ለዚህ ለተቀደሰ ወር በመድረሳችን አላህን እያመሰገንን የዘንድሮው ረመዳን ለመላዉ ሙስሊም ማህበረሰብ የሰላም ፤ የነጻነት ፤ የእድገ እንዲሁም ከጀሀነም እሳት ነጻ ወጥተን ጀነት የምንገባበት እንዲያደርግልን  አላህን እየለመንን እንደወትሮዉ ሁሉ በዚህ ረመዳን ጊዜያችንን ጥቅሙ በጣም ትንሽ በሆነ ከማባከን ተቆጥበን እያንዳንዳችንን ከአላህ ጋር የሚያቀራርቡንን  ስራዎች በመስራት እንደምናሳልፈዉ ተስፋ እያደረግን።

በእስር የሚገኙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና ሌሎች ከዚሁ ጋር በተያያዥነት በየክልሉ በእስር ላይ የሚገኙ ወንድምና እህቶቻችንን ከእስር ተፈተዉ አላህ በሰላም ከሚወዳቸዉና ከሚያፈቅራችዉ ቤተሰባቸዉ እና ማህበረሰባቸዉ ጋር እንዲቀላቅላቸዉ እየለመንን፤ ወሩን በሰላም ጀምረው በሰላም ከሚጨርሱትና ተጠቃሚዎች ከሚሆኑት ያድርገን።

                                                             ዳሪ ሀምዛ                                                                                                                                                                 ፕሬዚደንት