በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነዉ

 

የቆሼዉ  መንደር  አሰቃቂ  እልቂት

 

       በአዲስ  አበባ ከተማ በተለምዶ ቆሼ  እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ሰሞኑን በተከሰተዉ አሰቃቂና ዘግናኝ አደጋ በርካታ  ወገኖቻችን ህይወታቸዉን ማጣታቸዉ ይታወቃል። አደጋዉ በርካታ ታዳጊ ህጻናትን ያካተተና  ሙሉ ቤተሰብን በጅምላ የጨረሰ መሆኑ መላዉን ህብረተሰብ ክፉኛ አሳዝኗል ። ይህ ዘር እና ሀይማኖት፤ ልጅና አዋቂ ያለየ የእልቂት ክስተት ድህነትና ትንቢያ እንዲሁም ከቸልተኝነትና ከጥንቃቄ ጉድለት  ሳቢያ የተከሰተ አደጋ መሆኑን ሀገራዊና አለም አቀፍ የዜና ምንጮች ዘግበዉታል።

     በአደጋዉ ለተጎዱ ወገኖች በድር ኢትዮጵያ የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ፤ ለቤተሰቦቻቸዉም መጽናናትንና ብርታትን እንዲያገኙ ዱኣ እያደረግን (እየፀለይን) በዚሁ አጋጣሚ በድርና አባል ኮምዩኒቲዎች ተጎጂ ወገኖቻችንን ለመርዳት በሚደረገዉ ርብርቦሽ አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለብን ለማሳሠብ እንወዳለን። 

 

የበድር ቦርድ ዳይሬክተሮች                                                                              

ሰሜን አሜሪካ      

ማርች 19 2017