በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነዉ

click here to view pdf

 

ለኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ በሙሉ

ለመስጂድ  ግንባታ  የቀረበ  ጥሪ

 

       በድር ኢትዮጵያ  አለም አቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት በጉራጌ ዞን በሙሁር አክሊል ወረዳ  በተቃጠሉ የተለያዩ መስጂዶች ምትክ በአማካይ ቦታ የዎክሮን መስጂድ ግንባታ ጀምሮ  እንደነበር ይታወቃል። ሆኖም የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ የመብትና የእምነት ነጻነት ጥያቄ እንቅስቃሴ በይፋ ሲጀመር የድርጅቱም ሆነ የህዝባችን ትኩረትና ጥረት ሁሉ በዋነኛነት በእንቅስቃሴዉ ዙሪያ አትኩሮ  ስለነበር የመስጂዱ ሥራ  መሰረቱ ከተጣለና ምሰሶዉ ከቆመ በኋላ ግንባታዉ ተቋርጦ ቆይቷል።

     የተጀመረዉ መስጂድ ግንባታ ባለመጠናቀቁ በአካባቢዉ ነዋሪ ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ የሞራልና የስነልቦናዊ ጫና ፈጣሪ ከመሆኑ ባሻገር በድር ኢትዮጵያ የጀመረዉን ይህን ፕሮጀክት በአላህ (ሱወ ) ፈቃድ ከፍጻሜ ለማድረስ ቅድመ ሁኔታዎችን አመቻችቷል።

        ስለዚህ ለመላዉ ኮምዩኒቲ፤ የበድር ደጋፊዎችና እንዲሁም አህለል ኸይሮች ይህንን መስጂድ ፍጻሜ ላይ ለማድረስ እንድትተባበሩ የተለመደዉ እስላማዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

 

ለመስጂድ ግንባታ የምናወጣዉ ገንዘብ ለአኸይራ ቤታችን መገንቢያና  መሰረት ጣይ በመሆኑ በአዱንያም ሆነ በአኼራ ለመጠቀም እንሽቀዳደም።

 

በድር ኢትዮጵያ የዳይሬክተሮች ቦርድ

ሰሜን አሜሪካ

ዴሰምበር 14, 2016