በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነዉ  

16ኛዉ የበድር አመታዊ ኮንቬንሽን ባማረ መልኩ ተጠናቀቀ

    የበድር ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት 16ኛዉ አመታዊ ጉባኤ እጅግ ባማረና በደመቀ መልኩ በአላህ (ሱወ ) መልካም ፈቃድ በዉጤታማነት ተጠናቀቀ። ከጁላይ 28 እስከ 31, 2016 ለአራት ተከታታይ ቀናት በEAMAN ኮምዩኒቲ አዘጋጅነት በናሽፊል, ቴነሲ የተካሄደዉ ኮንቬንሽን  ከበርካታ  ስቴቶች በመጡ ታዳሚዎች እንዲሁም ከተለያዩ አካባቢ  በተሰባሰቡ ብርቅዬ ኡለማዎች በድምቀት ሲካሄድ ሰንብቷል።

     በጉባኤዉም በርካታ ጉዳዮች በጥልቀት የተዳሰሱ ሲሆን በበድር ፕሬዚዳንት በወንድም ዳሪ ሀምዛ በቀረበዉ ሪፖርት ሰፋ ያለ ዉይይት የተደረገ ሲሆን ከየ ግዛቱ በመጡ የኮምዩኒቲ መሪና ተወካዮችም ያላቸዉን ተሞክሮ ለህብረተሰቡ አቅርበዋል። ህብረተሰቡ የተሰማዉን ደስታና ለበድር ያለዉን ናፍቆትና አጋርነት በተክቢራ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል።

    በሀገራችን ኢትዮጵያ የተጀመረዉ ሰላማዊ የመብትና የእምነት ነጻነት ጥያቄን አስመልክቶ ሰፋ ያለ ዉይይት የተደረገ ሲሆን ሰላማዊ ትግሉን በጽናት እስከመጨረሻዉ ለዉጤት ለማብቃት ከዚህ በፊት ሲደርግ እንደነበረዉ ሁሉ ዳግም ሰላማዊ መፍትሄዎችን በማፈላለግ ለዉጤት ለማብቃት ጥረት ማድረግ እንደሚገባዉ ከህብረተሰቡ የተሰጡ  ጠንካራ  አስተያየቶች በመቀበል ድርጅቱም ያለዉን ጽኑ አቋም በድጋሚ ለህብረተሰቡ አረጋግጧል።

 

 

                            17ኛዉ የበድር ኮንቬንሽን በሳንዲያጎ, ካሊፎርኒያ  እንዲሆን ተወሰነ